የቅድስት ሥላሴ

Holy Trinity

ዛሬስ ተይዣለሁ

Lyrics

ዛሬስ ተይዣለሁ በፍቅርህ ስጦታ

ውለታህ ማርኮኛል የሰራዊት ጌታ

ከአመድ ያነሣኸኝ በትቢያ ተጥዬ

ውለታህ ከበደኝ ማረከኝ ጌታ'ዬ /2/

ያልሰጠኸኝ ነገር በዚህ ምድር የለም

ፍቅርህ ወሠን የለው ድንቅ ነው ዘላለም

እኔነቴን ሳስብ ምንድነኝ እላለሁ

ፍቅርህን ሳስተውል ሁል ጊዜ አለቅሳለሁ/2/

ለብቻዬ ሆኜ አምላኬን ሳስበው

ከሕሊና በላይ ውለታህ ብዙ ነው

የተጣለውን ሰው ማንሳት ያውቅበታል

ምስኪንን ሲያጽናና ከሁሉ ይበልጣል /2/

ሰው ነህ ተብያለሁ አንተ ሰው ስላልከኝ

ማን ያስታውሰኛል አንተ ባታከብረኝ

አትጣለኝ አንተ ሁሉም ያከብረኛል

ኃጢአቴን ባትቆጥር ለእኔ ይበቃኛል /2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening