✦
የቅድስት ሥላሴ
•Holy Trinity
አምላካችን ተመስገን
Lyrics
አምላካችን ተመስገን /2/
ለዛሬ ያደረስከን
አምላካችን ተመስገን /2/
ለዚህ ቀን ያደረስከን
በኃጢያት ስንማቅቅ በምህረትህ ጠራኸን
በዓለም ስንባዝን ነበር በይቅርታህ መራኸን
አምላክ ሆይ ተመስገን
ትዕግስትህ ብዙ ነው አያልቅም
ርህራሄህ የምንከፍልህ
ምን ይሆን ብዙ ነው ውለታህ
አምላክ ሆይ ተመስገን
ከቶ የማትፈልግ ከሰው ልጆች ወሮታ
ቸር ፈጣሪ ነህና ሥራህ ድንቅ ነው ጌታ
አምላክ ሆይ ተመስገን
ይቅር ባይ አምላካችን ሆይ አንተን እናመልካለን
ከመዓትህ ታግሠህ ሁሉንም ይቅር አልከን
አምላክ ሆይ ተመስገን
ኃጢያታችን ጨለማ ቢያደርገው ኑሮአችንን
በአንተ ተጎናጽፈናል የማዳንህን ብርሃን
አምላክ ሆይ ተመስገን
ስላደረክልን ሁሉ ስለ ግሩም ሥራህ
የራስህን እንስጥህ ተመስገን እንበልህ
አምላክ ሆይ ተመስገን
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.