✦
የቅድስት ሥላሴ
•Holy Trinity
አባታችን ሆይ
Lyrics
አባታችን ሆይ የምትኖር በሰማይ
መንግስትህ ትምጣልን ክብርህን እንድናይ /2/
ፈቃድህ በሰማይ ሕይወት እንደሆነ
እንዲሁም በምድር ሰላምህን ስጠን /2/
ስጠን ለዛሬ የዕለት ምግባችንን
በደላችንንም ይቅር እንድትለን /2/
ጌታ ሆይ አታግባን ከክፉ ፈተና
አንተ ካልረዳኸን ኃይል የለንምና /2/
ኃይልና ምስጋና መንግሥትም የአንተው ናት
አሜን ለዘለዓለም ይሁንልን ዕረፍት /2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.