የቅድስት ሥላሴ

Holy Trinity

አምላካችን ቅዱስ ነህ

Lyrics

አምላካችን ቅዱስ ነህ ፈጣሪያችን ቡሩክ ነህ የዘለዓለም አምላክ ነህ /2/

የአዳም ልጅ ከትቢያ /2/ ወደ ነበረበት

መልሶም ከአፈር እንዲሆን ከመሬት

በተናገርከው ቃል ባዘዝከው መሠረት

እንደ ጐርፍ መጥተህ ትወስዳለህ ድንገት /2/

ከሕልም የረዘመ /2/ ሕይወት የለንም

ማለዳ እንደሚበቅል እንደ ጠዋት አረም

ጠውልጐ እንደሚደርቅ እንደዚህ አለም /2/

ሕይወትህ ናትና /2/ እንደ ጠዋት ጤዛ

ረግፎ ለሚቀር ውበትና ለዛ

እባክህ የሰው ልጅ ኃጢአትን አታብዛ/2/

ዕድሜያችን ሰባ ዓመት ቢበዛ ሰማንያ

በመከራ ያልቃል እርሱም በዓለም ዙሪያ

እኛም እናልፋለን በጭራሽ ሳንሠራ

በራስ ተሸክመን የኃጢአት አዝመራ /2/

የመከራ ዓመታት አሳልፈናል

ፍርድን በመፍራት ተሸብረናል

እባክህ ጌታ ሆይ በችሮታህ ሥራ

ለአገልጋዮችህ አምላከ ሆይ እራራ /2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening