✦
የቅድስት ሥላሴ
•Holy Trinity
የሰው ልጅ በኃይልህ
Lyrics
የሰው ልጅ በኃይልህ ፈጽሞ አትመካ /2/
አንድ አምላክ አለና በኃይሉ ኃይልን የሚለካ /2/
ኃይል እንደ ሶምሶን ከአምላክ ሲሰጥ እንጂ /2/
በጉልበት መመካት ለማንም አይበጅ/2/
ሰናክሬም ቢነሳ በሕዝቅያስ ላይ /2/
የደረሰበትን አልሰማህም ወይ /2/
ጎልያድ በኃይሉ ዳዊትን ቢንቀው /2/
አዋረደው እንጂ ኃይሉ ምን ጠቀመው/2/
እንደ ዳታንና እንደ አቤሮን አይሆንም በግድ /2/
ተመርጦ ነው እንጂ ለክብር በአምላክ ፈቃድ /2/
ክህነትን ለአሮን ሕግንም ለሙሴ /4/
ከሰው ሁሉ መርጠው ሰጣቸው ስላሴ /2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.