✦
የቅድስት ሥላሴ
•Holy Trinity
ሕይወቴ ቢመራ
Lyrics
ሕይወቴ ቢመራ ጌታ በቃልህ
ጣፋጭ ይሆን ነበር ሲያድሰኝ ፍቅርህ
የአንተ ጸጋ ጌታ ስለበዛልኝ
ጨለማው ተገፎ ብርሃንህ መራልኝ
በሕይወቴ በዘመኔ
ደስ የሚለኝ ለእኔ
በወንጌል ማመኔ
ወዴት እሔዳለሁ የእጅህ ጥበብ ሆኜ
ፍቅርህ እያደሰኝ ሞተህልኝ ድኜ
ምን አይነት መውደድ ነው ለእኔ አንተ ያለህ
ምን ይከፈለዋል ለፍፁሙ ፍቅርህ
ምን አይነት መውደድ ነው አንተ ለእኔ ያለህ
ምን ይከፈለዋል ለፍፁሙ ፍቅርህ
ደጅህ ላይ ተይዤ ደጅህ ላይ ልሙት
ቃልህን ልጠብቅ በፍፁም ፍርሐት
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.