✦
የቅድስት ሥላሴ
•Holy Trinity
በሞት ጥላ ወድቀን
Lyrics
በሞት ጥላ ወድቀን ስንንከራተት /2/
በረቀቀው ፍቅሩ ዋጀን ከጥፋት /2/
በጎልጎታ የታየው ግሩም መድኃኒት
ሃሌ ሃሌ ሉያ ለአንተ ለኃያሉ ጌታ /2/
ስለ እኛ ተዋረድክ በጎልጎታ
የሞት ሽክም ከብዶን በጣር ስንባዝን /2/
ወረደ ከሰማይ መጣ ሊያድነን /2/
ከባርነት መንፈስ ሊገላግለን
ምንም ባልበደለ ምንም ባላጠፋ /2/
ሁሉን ማድረግ ሲችል ደካማ የሆነው /2/
ሕይወትን ሊያድለን ሰለወደደ ነው
እስቲ አስተውሉ የፍቅሩን ብዛት /2/
በመስቀል ተሰቅሎ እኛን ያዳነበት /2/
ምንም አቻ የለው የጌታ ቸርነት
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.