የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም

St. Virgin Mary

እመቤቴ የአምላክ እናት

Lyrics

እመቤቴ የአምላክ እናት

ላመስግንሽ ቀን ከሌሊት

ለልጅሽም ክብር ውዳሴ

ታቀርባለች ዘወትር ነፍሴ /2/

ልቤ ተነሳሳ ተቀኘ ለክብርሽ

በፍጹም ትህትና ሊያመሰግንሽ

ጽዮን መጠጊያ ነሽ የአብርሃም ድንኳን

የታጠረች ተክል እመብርሃን

የለመለመች መስክ አምላክ የመረጣት

የጽላቱ ኪዳን ታቦቱ ድንግል ናት

የሰማይ የምድር ንግሥት ናትና

ክብር ይገባታል ዘወትር ጠዋት ማታ

አደራሽን ማርያም የሁሉ እናት

በምልጃሽ አስቢኝ ኋላ ስራቆት

ያንን የእሳት ባሕር አሻግሪኝ ድንግል ሆይ

እንዳልወድቅ እንዳልሞት ከቶ እንዳላይ ስቃይ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening