የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም

St. Virgin Mary

ጐስዐ ልብየ

Lyrics

ጐስዐ ልብየ ቃለ ሠናየ /2/

ወአነ አይድዕ ቅዳሴሃ ለማርያም /4/

እኔስ የማርያምን ውዳሴዋን እናገራለሁ

እንደ አባቴ ዳዊት በበገና እዘምራለሁ

ቀን ከሌሊት ሳልል ለምሥጋና እተጋለሁ

የኃጢአቴ ቁስል እንዲፈወስ እጮሃለሁ

ምርኩዜ ነሽና እመቤቴ በአንቺ እመካለሁ

ኦ እመቤቴ በእውነት እንወድሻለን

የእውነተኛ መብልን ክርስቶስን ወለድሽልን

ምክንያተ ድሂን ሆይ ድንግል ማርያም የአምላክ መገኛ

በአማላጅነትሽ በመታመን እንጮሃለን እኛ

ምሕረትን አሰጪን ኪዳነምሕረት የዓለም መዳኛ

ስለቸርነትሽ እመቤቴ ለእኔ እናቴ ነሽ

ስለንግስትነትሽም እመቤቴ ነሽ

ዝናባት ሳያጠጡት አየራትም ሳያሳድጉት

ሰማያዊ እንጀራ የሰጠሽን ቤቴልሔማዊት

ቅድስተ ቅዱሳን የኖህ መርከብ የአምላክ እናት

ቃና ዘገሊላ በሰርግ ቤት በዚያ ተገኝተሽ ሳለሽ

ውሃውን ወደወይን ባንቺ ምልጃ እንዳስለወጥሽ

ዛሬም የኔ ሕይወት ወይኑ አልቆ ባዶ ሆኗልና

አንቺ የአምላክ እናት ንጽሕት ቅድስት ርኅርኅተ ህሊና

ሕይወቴን አድሰሽ ቀድሰሽው ሙይው በምስጋና

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening