✦
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
•St. Virgin Mary
በውዳሴሽ ልትጋ
Lyrics
በውዳሴሽ ልትጋ ሥምሽ ግርማ ያለው /2/
እመቤቴ ኧኸ እመቤቴ ስልሽ እውላለሁ /2/
ከልቤ አቀርባለሁ ምሥጋና ለስምሽ
መለመኛዬ ነው ፅኑ ቃል ኪዳንሽ
በሰላምታ ድምፅሽ ያልጸና ማን አለ
ፅንሱ በማሕፀን በደስታ ዘለለ
ማርና ወተት ነው የስምሽ ስያሜ
እመቤቴ ስልሽ ይቀላል ሽክሜ
ቅኔ ማሕሌቱ ሰዓታት መዝሙሩ
ያመሰግኑሻል ምድርና ጠፈሩ
እናቱ ነሽና አንቺ ለአዶናይ
ማለድኩኝ ከፊትሽ ይቅርታውን እንዳይ
ሰዓሊለነ ብዬ ይኸው ተርፌአለሁ
በአንቺ ተደግፌ ነገም እኖራለሁ
ነይ ነይ እልሻለሁ እንደ ካሕናቱ
በሰዓታት ፀሎት ቆሜ በሌሊቱ
ዝም አልልም እኔ አወድስሻለሁ
የዓለምን መከራ እረሳብሻለሁ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.