✦
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
•St. Virgin Mary
ማርያም ማርያም በሉ
Lyrics
ማርያም ማርያም በሉ
የተጨነቃችሁ ያዘናችሁ ሁሉ
ቅድስት ማርያምን አዛኝቷን ጥሩ
የጌታዬ እናቱን አዛኝቷን ጥሩ
ነይ በሏት ትመጣለች /2/
ሀዘን ጭንቀትን ትገላግላለች
ድንግል ማርያም ፀምረ ጌዲዎን ነሽ
የታቦር ተራራ
የአባ ጊዮርጊስ
የአረጋኖን ሙሽራ
በአዛኝነትሽ
ስንቄ የሆንሽኝ
ዛሬም ፈጥነሽ ስሚኝ
ድንግል አትርሺኝ
ድንግል ማርያም ብሥራተ ገብርኤል
የሚካኤል ፋና
አክሊለ ጊዮርጊስ
የሱራፌል ጽንሐሕ
ነይ ፈጥነሽ ድረሽ
ተጨንቀናልና
ድንግል ማርያም ፍጥረታት በሙሉ
ያመሰግኑሻል
የሕይወታችን በር
ድንግል ናት ይሉሻል
እኛ እንጠራሻለን
ጌታ ስለሰጠን
ሲጨንቀን ሲጠበን
ላንቺ ልጆች አድርጎ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.