የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም

St. Virgin Mary

ለማርያም ድንግል

Lyrics

ለማርያም ድንግል መንበረ ተድላ /2/

ወሪዶ ገብርኤል ምድረ ገሊላ

ትወልዲ ወልደ ለድንግል ይቤላ

አዲስ ዜና ይዞ ለማርያም ድንግል

ሰማያት ሰንጥቆ መጣ ገብርኤል

ድንግል ከአንቺ ጋራ አምላክ ስለሆነ

ምክንያት አንቺ ሆንሽ ዓለም ሁሉ ዳነ

መዝገበ ጽድቅ ነሽ ምስጋና ይገባሻል

ሰማያዊ ጌታን ድንግል ሆይ ወልደሻል

መመኪያና ምርኩዝ ለእኛ ልትሆኝን

በስዕለት ወለዱሽ ሐናና ኢያቄም

በማይደክም ልሳን በመላዕክት ቋንቋ

ትመሰገናለች የእኛ እናት በራማ

ጌታችን ተጸንሶ በማኅጸን ሳለ

የመላዕክት ዝማሬ ትሰማ ነበረ

የነቢያት ትንቢት ፍጻሜ አገኘ

ገብርኤል ተልኮ መድኃኒት ተገኘ

ንጹሕ ዘር ከሆነች ከእመቤታችን

በፍቃዱ ወርዶ ተወለደልን

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening