የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም

St. Virgin Mary

ንዒ ንዒ

Lyrics

ንዒ ንዒ ማርያም ንዒ ንዒ

ድንግል ሆይ ንዒ ንዒ

ያን የእሳት ባሕር ከቶ እንዳላይ

በሐመረ ኖህ የተመሰልሽ

በአሮን በትር የተመሰልሽ

የምሥራቋ በር /2/ ቶሎ ድረሽ

በተራራማው በኤፍሬም ሀገር

እንግዳ የሆንሽ ለኤልሳቤጥ በክብር

ነይልኝ ወደእኔ /2/ ካንቺ ጋር ልኑር

ዓለም ከብዶብኝ ተጨንቄያለሁ

ኃዘን በዝቶብኝ ብቸኛ ሆኛለሁ

ኧረ ነይ ድንግል ሆይ /2/ እጠራሻለሁ

ጥበቡ አንቺ ነሽ ለሲሎንዲስ

ነይ ብሎ የሚጠራሽ ሱላማጢስ

አትጥፊ ድንግል ሆይ /2/ በእጅሽ ልታሰር

ምሥጢር የገለጽሽ ለሕርያቆስ

ፈጥነሽ ያማለድሽ በቤተ ዶኪማስ

ነይልኝ እናቴ /2/ ልቤ ይፈወስ

ድንግል ቀርባለች ጩኸቴን ሰምታ

የኃጢአቴ ገመድ እስሩ ተፈታ

አከብራታለሁ /2/ ልጇ በእልልታ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening