የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም

St. Virgin Mary

ሰአሊ ለነ ቅድስት

Lyrics

ሰአሊ ለነ ቅድስት እንልሻለን /2/

እንደ ኤፍሬም እንደ አባታችን

ለምኝልን እመቤታችን

ተስፋችን ነሽና ለፍጥረት ዓለም

እየተመኩብሽ እስከ ዘለዓለም

ኃጢያታቸው ተደምስሶላቸው

በአንቺ ጸሎት ዳነች ሕይወታቸው /2/

ስምሽም ስልጡን ነው በእግዚአብሔር መንበር

ቃልኪዳን ገባልሽ ዓለሙን ሊምር

በአንቺ ጸሎት ይተማመናሉ

ጠዋት ማታ ቅድስት ሆይ ይላሉ /2/

ዓለም ስትዋጋን በምኞት ስለት

ነፍሳችን ስትዝል ሲከብዳት ኃጢአት

ጨልሞብን ግራ ሲገባን

ብርሃናችን ነይ እናታችን /2/

የልባችን ኀዘን እጅጉን ከብዶናል

ኃጢአታችን በዝቶ መቆም ተስኖናል

እንደ ኤልሳቤጥ እንደ ዘመድሽ

ደስ አሰኚን ይሰማ ድምፅሸ /2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening