የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም

St. Virgin Mary

ሐረገወይን

Lyrics

ሐረገ ወይን /4/ እመብርሃን

የጸጋ ሁሉ ምንጭ የሕይወቴ ተስፋ

እስኪ ላመስግንሽ ሳላፍር በይፋ

ምርኩዜ ልበልሽ ጥላ ከለላዬ

የእኔ መመከቻ ዕንቁዋ ጋሻዬ

ሐረገ ወይን

መልካሚቱ ሽቱ የሕሙማን ፈውስ

የአብ ቃል እናቱ ድንቅ ዕፀ ጳጦስ

መዓዛሽ ተስማሚ የሕይወት ምግብ

የቅንነት መዝገብ የሰላም ርግብ

ሐረገ ወይን

የአቤል መሥዋዕት የዳዊት መዝሙር

የአሮን ክህነት ነሽ ፀአዳ ፀምር

የስደተኞች ቤት ማረፊያ ድንኳን

የልባችን ደስታ እመቤታችን

ሐረገ ወይን

እንደ ወይን እንደዘለላ /2/

የጻድቃን እመቤት የጽድቃችን ጥላ

ስምሽ የጣፈጠ ግሩም ነው ወለላ

ማርያም ርግብየ ይቤላ /2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening