✦
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
•St. Virgin Mary
አንቺ የወይን ሐረግ
Lyrics
አንቺ የወይን ሐረግ ድንግል ልምላሜሽ የበዛ
ምግብ ሆኖ /2/ ተሰጠን ፍሬሽ ለእኛ ቤዛ
በአንቺ ሰማይነት ድንግል የወጣው ፀሐይ
ብርሃን ነው /2/ ለጻድቃን ስሙም አዶናይ
ፊደል ትመስያለሽ ድንግል ወንጌል ትወልጃለሽ
ለመላእክት /2/ የማይቻል ነበልባሉን የቻልሽ
የመሶብ ምሳሌ ድንግል የመና መገኛ
በሥጋችን በነፍሳችን እንዳንራብ አንቺ አለሽን ለእኛ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.