የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም

St. Virgin Mary

በምን በምን

Lyrics

በምን በምን እንመስላት ድንግል ማርያምን/2/

ምሳሌ የላትም የላትም ክብሯን የሚመጥን/2/

የሙሴ ጽላት ነሽ የምሕረት ቃል ኪዳን

የያዕቆብ መሰላል የአብርሃም ድንኳን

የብርሃን መውጫ የኖኅ ድንቅ መርከብ

የመላዕክት እኅት የሩኅሩኃን ርግብ /2/

የሰሎሞን አክሊል የአሮን በትር

የዕዝራ መሰንቆ የጌዴዎን ጸምር

ድንግል እመቤቴ ናት የጻድቃኖች በር

ሆና የተገኘች የአምላክ ማኅደር /2/

የቅዱሳን እናት የዓለም ንግሥት

ችላ ተሸከመች መለኮት እሳት

ብርሃን ትሁነን ጨለማን ገላልጣ

አማልዳ ታስምረን ከዚህ ዓለም ጣጣ /2/

ከማር ይጣፍጣል የድንግል መዓዛ

አምላክን አቅፋለች በሁለት እጇ ይዛ

ዓለም ሁሉ የዳነው በልጅሽ ነውና

እናታችን ጽዮን ይድረስሽ ምስጋና /2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening