✦
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
•St. Virgin Mary
ትህትናሽ ግሩም ነው
Lyrics
ትህትናሽ ግሩም ነው ደግነትሽም /2/
እናቱ ሆነሻል ለመድኃኒዓለም /2/
ንፅሕት ስለሆንሽ እመቤቴ እመቤቴ
እንከን የሌለብሽ
የፍጥረታት ጌታ
በአንቺ ያደረብሽ
የድንግል መመረጥ
ዜናው አስገረመን
እሳቱን ታቀፈች
የማይቻለውን
ምርኩዜ ልበልሽ እመቤቴ እመቤቴ
ጥላ ከለላዬ
ጋሻዬ ነሽ አንቺ
ለእኔ መመኪያዬ
በዓለም እንዳልጠፋ
ሕይወቴ መሮብኝ
እንደ ወይን አጣፍጭው
ማርያም ድረሽልኝ
የምስራቅ ደጃፍ ነሽ እመቤቴ እመቤቴ
የሁላችን ደስታ
እሙ ለፀሐየ ጽድቅ
የሁሉ ጠበቃ
ድንግል የድል አክሊል
ድንግል የጽድቅ ስራ
ድንግል መሰላል ነሽ
የተዋሕዶ ተስፋ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.