✦
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
•St. Virgin Mary
ለማርያም
Lyrics
ለማርያም /2/
እንዘምራለን ለዘለዓለም /2
የተዘጋች ደጅ ለዘለዓለም
ሕዝቅኤል ብሏል
ንጽሕት ናት በእውነት
በፍጹም ድንግል
አብነት አርገን
እኛም እርሱን
በፍጹም ፍቅር እንዘምራለን 12/
የዋሂት ርግብ
ሰላም አብሳሪ
ለጨለማ ሕይወቴ
ብርሃንን አብሪ
እማጸንሻለሁ
ድንግል ለነፍሴ
ለዘለዓለም
አደራ ድንግል አንቺ ነሽ ዋሴ /2/
እጅግ የበዛ ነው ለዘለዓለም
ያለኝ ፍቅር
አይወሰንም
አይነገርም
በእርሷ ደስ ይለኛል
ሐሴት አደርጋለሁ
ስሟን እየጠራሁ እዘምራለሁ /2/
ነይ ነይ ስላት ለዘለዓለም
ቀንና ሌሊት
አትለየኝም
ለእኔስ ቅርቤ ናት
እፁብ እፁብ ብለው
አመሰገኗት
ክብሯን ሊገልጹት ቢያጥራቸው ቃላት /2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.