✦
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
•St. Virgin Mary
የወርቅ መሰላል ነሽ
Lyrics
ድንግል ማርያም የወርቅ መሰላል ነሽ
መሰላል ነሽ የወርቅ መሰላል ነሽ
ሰውና አምላክን ያገናኘሽ
አባታችን ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ /2/
አሸልቦት እንቅልፍ ተኝቶ ከጤዛ
ከምድር እስከ ሰማይ የምትደርስ መሰላል
ምሳሌሽን አየ ማርያም ድንግል
መላእክት ሲወጡ ሲወርዱ ከሰማይ /2/
እንዳየ ያዕቆብ ተኝቶ መንገድ ላይ
ተስፋ አድርጎ ሲኖር የሰላሙን ዘመን
ይኸው ተፈፀመ በአንቺ በእናታችን
በአንቺና በልጅሽ ሆነልን ሰላም /2/
በአንቺ ተፈጸመ የያዕቆብ ሕልም
ሰውና መላዕክት ተለያይተው ሲኖሩ
በልጅሽ መወለድ በአንድ ላይ ዘመሩ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.