✦
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
•St. Virgin Mary
ወዳጄ ሆይ
Lyrics
ወዳጄ ሆይ እነሆ ውብ ነሽ
የታተመች ፈሳሽ እንከን የሌለሽ
የተዘጋች ደጅ ንጽሕት አዳራሽ
ሕዝቅኤል ያየሽ የምስራቋ በር
ማንም ያልገባባት ከአምላክ በስተቀር
የልዑል ማደርያ አማናዊት መቅደስ
ስለንጽሕናሽ ምስጋናን እናድርስ
ሁለቱንም የሆንሽ እናትና ድንግል
ማኅደረ መለኮት ወላዲተ ቃል
ያለዘርአ ብዕሲ በኅቱም ድንግልና
አምላክን የወለድሽ ሐመልማለ ሲና
ምስራቀ ምስራቃት ድንግል ሆይ አንቺ ነሽ
ጨረቃን የምትመስይ ፀሐይን የወለድሽ
የማለዳ ብርሃን ለዓይን የምትሳሺ
ጽዮን እናቴ ሆይ ከጎኔ አትሽሺ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.