የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም

St. Virgin Mary

ቀስተ ደመናው

Lyrics

የኖኅ ቃል ኪዳኑ ምልክት ዓርማው

የመዳኑ ምስጢ የሰላም ተስፋው

እመቤቴ አንቺ ነሽ ቀስተ ደመናው /2/ /2/

አንቺ የአሮን በትር ሳይተክሏት ያደገች

የማክሰኞ እርሻ ያለዘር ያፈራች

የሲና ሐመልማል የተዋሕዶ ምሥጢር

ክብርት እመቤቴ ሀገረ እግዚአብሔር /2/

የዳዊት መሰንቆ የያሬድ ጸናጽል

የደካሞች ምርኩዝ የሰሎሞን አክሊል

ሰላሜ ተስፋዬ የኀዘኔ ደራሽ

የጽዮን ተራራ መሸሸጊያዬ ነሽ /2/

የኤልሳዕ ማሰሮ ጨው የተገኘብሽ

የሕዝቅኤል ራዕይ ንጽሕት አዳራሽ

አንቺ የዓለም ተስፋ የመዳኑ ብሥራት

አንቀጸ ብርሃን ነሽ የአማኑኤል እናት/2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening