✦
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
•St. Virgin Mary
ሰላም ለኪ ለኖኅ ሐመሩ
Lyrics
ሰላም ለኪ /2/ ለኖኅ ሐመሩ
ሰላም ለኪ ለአሮን በትሩ
ሰላም ለኪ ለቅዱስ ዳዊት መሰንቆ መዝሙሩ
ሰላም ለኪ ለጌዴዎን ፀምሩ
ሰላም ለኪ ለሰሎሞንም መንበረ ክብሩ
ሰላም ለኪ ለፍሬ ስብሐት መፆሩ /2/
እመ እግዚአብሔር ጸባኦት ሰላም ለኪ
ሰላም ለኪ ሠረገላሁ ለአሚናዳብ
ሰላም ለኪ መና ያለብሽ ንጹሕ መሶብ
ሰላም ለኪ ያዕቆብ ያየሽ በሎዛ
ሰላም ለኪ የይስሐቅ መዓዛ /2/
እንዘ ንሴፈዎ ለበረከትኪ
ዘምስለ አምኃ ንሰግድ ለኪ /2/
ሰላም ለኪ ሕብስተ መና ዘእስራኤል
ሰላም ለኪ የሰማዕታት ንጹሕ አክሊል
ሰላም ለኪ ዕፀ ጳጦስ ዘሲና
ሰላም ለኪ የኤልያስ መና /2/
እንዘ ንሴፈዎ ለበረከትኪ
ዘምስለ አምኃ ንሰግድ ለኪ /2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.