የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም

St. Virgin Mary

በዝናመ ንጽሕኪ

Lyrics

በዝናመ ንጽሕኪ ሐረገወይን ፀገየ /2/

ወሮማን /2/

ወሮማን ሐዋዘ ፈረየ /2/

እመቤቴ ማርያም ሆይ አንቺን የማይበት /2/ ምን ዓይን አለኝ /5/ ፍቅርሽ አይለየኝ/2/

ለአዳም ተስፋ የሆንሽው ማርያም እመቤት /2/ አማልጅኝ ቶሎ ብለሽ /3/ ሳልጠፋብሽ ልጅሽ /2/

የዳዊት መሰንቆ ነሽ የኢያሱ ሐውልት በምን እንመስልሽ /3/ ወደርም የለሽ /2/

እመቤቴ ጥላዬ ሁኚልኝ ከለላዬ /2/ ያለአንቺ ማን አለኝ /3/ አለሁሽ/ህ/ በይኝ /2/

አዳምና ሔዋን ከገነት ተሰደው /2/ ማርያም አንቺ ነሽ /3/ የመዳን ተስፋቸው

የእግዚአብሔር አብ ሙሽራ ወልድን የወለድሽ የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ /3/ ንጽሕት አዳራሽ

የሰሎሞን አክሊል የታጠረች ተክል የአሮን ካኅን ልብስ /3/ የወርቅ ጸናጽል

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening