✦
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
•St. Virgin Mary
ለምኚ
Lyrics
ለምኚ ድንግል ለምኚ /2/
ለኃጥኣን /3/ አይደለም ለጻድቃን /2/
ለምኚ ታላቅ ስጦታዬ
አዛኝ ሩኅሩኅ ነሽ የጌታዬ እናት
ጸጋን የተሞላሽ የአምላክ ማደሪያ
ለምነሽ አስምሪን አማናዊት ጽዮን
ከእኔ አትለይኝ
ለምኚ ኃዘንሽ አዘኜ
ለእኔ ይሁን ድንግል የተንከራተትሽው
በሀገረ እስራኤል ትእግስትሽን ሳየው
ልቤ ይመሰጣል የኃዘን እንባ ጎርፍ
ዓይኔን ይሞላዋል
ለምኚ በቀራንዮ አንባ
በዚያ የፍቅር ቦታ በእግረ መስቀሉ ስር
ከክርስቶስ ጌታ ለእኛ ተሰጥተሻል
እናት እንድትሆኝን ልጆችሽ ነንና
ምልጃሽ አይለየን
ለምኚ አንደበቴን ጌታ
በምስጋና ምላው ደስ ይበልሽ ብዬ
እኔም ላመስግናት አንደበቴን ጌታ
በምስጋና ምላው ደስ ይበልሽ ብዬ
እኔም ላመስግናት
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.