የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም

St. Virgin Mary

ስምሽን ጠርቼ

Lyrics

ስምሽን ጠርቼ መቼ አፍራለሁ

ማርያም ብዬ መች እወድቃለሁ

የምጽናናበት ስምሽ ነውና

ድንግል ሆይ ላቅርብ ላንቺ ምስጋና

ጨለማ ውጦኝ በጠላት ሀገር

ለዘመናትም ስቸገር ስኖር

ዲያብሎስ ማርኮ ሲያሰቃየኝ

የዓለሙን መድኅን ወለድሽልኝ

ካባቶቼ ርስት ከሀገር ወጥቼ

በአሕዛብ ሀገር ስኖር ተሽጬ

ደርሰሽ አጽናንተሽ አከበርሽኝ

ብቸኝነቴን አስረሻኝ

ድንኳኑ ሞልቶ ሰዉ ታድሞ

አስተናባሪው በጭንቀት ቆሞ

ምን አቀርባለሁ ብዬ ስቸገር

ምልጃሽ ደርሶልኝ ዳንኩኝ ከማፈር

ያሰብኩት ሃሳብ ደመና ሆኖ

ቢበተንብኝ እንደ ጉም በኖ

ይሆናል ያልኩት ሳይኖን ቢቀርም

በእመአምላክ እኔ ተስፋ አልቆርጥም

እናት አባቴ ባያስታውሱኝ

ይህቺ ዓለም ንቃ ገፍታ ብትተወኝ

አንቺ ካለሺኝ ምን እሆናለሁ

አውሎ ንፋሱን ባህሩን አልፋለሁ

ጠላቴ ደርሶ ቢያንገላታኝም

መከራ አብዝቶ ቢያስጨንቀኝም

አላቋርጥም ያንቺን ምስጋና

ውለታሽ ድንግል አለብኝና

ክፉዎች ደርሰው ቢዝቱብኝ

አንቺን መውደዴን አያስተዉኝ

በአሕዛብ መሀል ስምሽን ስጠራ

መከታ ሁኚኝ እናቴ አደራ

ጠላቴ ደርሶ ቢያንገላታኝም

መከራ አብዝቶ ቢያስጨንቀኝም

አላቋርጥም ያንቺን ምስጋና

ውለታሽ ድንግል አለብኝና

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening