✦
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
•St. Virgin Mary
በኃዘኔ ደራሽ ነሽ
Lyrics
በኃዘኔ ደራሽ ነሽ በጭንቀቴ በችግሬ ደራሽ ነሽ
የአምላኬ እናት የጌታዬ እናት ድንግል እመቤቴ ወላዲተ ቃል/2/
መልካሚቱ ርግብ ድንግል እመቤቴ
ማርያም እናቴ ነሽ ድንግል እመቤቴ
ከፍጥረታት ሁሉ ድንግል እመቤቴ
ገናና ነው ክብርሽ ድንግል እመቤቴ
የኀዘኔ መጽናኛ ድንግል እመቤቴ
እንባዬን አባሽ ነሽ ድንግል እመቤቴ
ዋሻ መጠለያ ድንግል እመቤቴ
የዘለዓለም ቤቴ ድንግል እመቤቴ
መንገድ ስሄድ ስንቄ ድንግል እመቤቴ
መጠጤ ነሽ ምግቤ ድንግል እመቤቴ
እመ አምላክ ስጠራሽ ድንግል እመቤቴ
ይጠፋል ረሀቤ ድንግል እመቤቴ
የእናትነትሽን ድንግል እመቤቴ
ፍቅርሽን አየሁት ድንግል እመቤቴ
ጎጆዬን ስትሞይው ድንግል እመቤቴ
ባዶ የሆነውን ድንግል እመቤቴ
አንቺ እያለሽልኝ ድንግል እመቤቴ
ምን እሆናለሁኝ ድንግል እመቤቴ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.