✦
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
•St. Virgin Mary
በጎ መዓዛ
Lyrics
በጎ መዓዛ ሽታዬ ነሽ
በሰው ሁሉ ፊት ዘመርኩልሽ
ባንቺ ጣፈጠ አልጫነቴ
እጠራሻለሁ ነይ እመቤቴ
ምሳሌ የሌለሽ ነይ እመቤቴ
ዘመዴ ነሽ ያን ክፉ ዘመን ያለፍኩብሽ
በፍቅርሽ እሳት ልቤ ነደደ
እናትነትሽን ስለወደደ
የሰውስ ጉልበት ነይ እመቤቴ
ምን ይረባኛል ሰረገላዬ መች ያድነኛል
ከተሰወረ ክፉ መከራ
እድናለሁኝ አንቺን ስጠራ
ለስንፍናዬስ ነይ እመቤቴ
መቼ ልክ አለው ስለበደሌ እተክዛለሁ
ለአነጋገሬ ማጣፈጫ ነሽ
ተሰምቻለሁ ድንግል ሆይ
የረሃቤ መርሻ ለታመመ ሰው ነሽ መፈወሻ
ለመንገዴ ስንቅ ነይ እመቤቴ
የተማጸነ በስምሽ አምኖ
ማን አፍሮ ያውቃል ፊትሽ ለምኖ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.