✦
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
•St. Virgin Mary
አስታርቂኝ
Lyrics
አስታርቂኝ ድንግል ማርያም /2/
ከልጅሽ /3/ ከመድኃኔዓለም
አስታርቂኝ ኃጢአትን ሰርቼ ገፍቼ ወጥቼ
የቤቴን ገበታ ልበላ ተመኘሁ የእንስሳት ገፈራ
አስታርቂኝ ወደ አባቴ ልሂድ አሁን ተነሥቼ
ይቅርታ ልጠይቅ እግሩ ስር ወድቄ
ልጅነቴ ቀርቶ አድርገኝ ባርያህ ከሞያተኞችህ እንደ አንዱ ቆጥረህ
አስታርቂኝ ገና ሩቅ ሳለሁ አባቴ አይቶኝ
ወደእኔ ሮጦ አቅፎ ነው የሳመኝ
ጠፍቶ የነበረው ተገኘልኝ አለ
ሞቶ የነበረው ደግሞ ሕያው ሆነ
አስታርቂኝ ሀብትን ተካፍዬ ከገዛ አባቴ ከቤቴ ኮበለልኩ ይሻለኛል ብዬ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.