የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም

St. Virgin Mary

እመ አምላክ ሙሽራ ነሽ

Lyrics

እመአምላክ ሙሽራ ነሽ ለቃል ማደሪያ ለመሆን የበቃሽ ኧኸ /2/

አስራ ሁለት ዓመት ቤተ መቅደስ የኖርሽ የመመረጥ ጸጋ ከጌታ ያገኘሽ

በአብሣሪው መልአክ እጹብ ድንቅ ዜና ከሰማይ መጣልሽ አቋርጦ ደመና

በስድስተኛው ወር ተልኮ ገብርኤል ቤተመቅደስ ገባ ሊያበስራት ለድንግል

በልዩ ሰላምታ ሰላም ለኪ ያለሽ የክርስቶስ እናት በጣም ደስ ይበልሽ

መላእክት በሰማይ ያመሰግኑሻል ክብር ለአምላክ እናት ይድረሳት ይሉሻል

በማሕፀንሽ ቢያድር የሠራዊት ጌታ ለመሆን ተመረጥሽ የአምላክ ቅዱስ ቦታ

የፈጣሪ እናት መሆንሽን ተረድቶ ሰላም ላንቺ ይሁን አለሽ እጅ ነሥቶ

ከፍጡራን ሁሉ አንቺ ትበልጫለሽ ገብርኤል ተልኮ ደስታን አበሰረሸ

ምንኛ ድንቅ ነው ድንግል የአንቺ ብሥራት ጌታን ትወልጃለሽ የሚል ቃልን መስማት

ይሁንልኝ ብለሽ ቃሉን የተቀበልሽ ድንግል ሆይ እናቴ እጅግ ልዩ እኮ ነሽ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening