✦
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
•St. Virgin Mary
ወደ ምሥራቅ እዩ
Lyrics
ወደ ምሥራቅ እዩ ወደ ፀሐይ መውጫ
ድንግልን ክበቧት እንበል ሃሌ ሉያ
አንቺን ለማመስገን ልቡናዬ ይብራ
በብርሃን ተከበሽ ወርቅ ለብሰሽ
ተፈሥሒ ድንግል ከሴቶች ሁሉ
ኦ ቤተልሔም አብ መረጠሸ
ካንቺ ተወለደ እመቤታቻን ድንግል ሆይ
ልጆችሽ መድኃኔዓለም ዘወትር ይጠሩሻል
ውዳሴ ማርያም ቅዱሳኑ ሁሉ ስምሽን ለልጅ ልጅ
ለአምላክ እናት ለአዛኝት እልል እንበል እንዘምርላት /2/
ዙሪያሽን ከበዋል ወገኖች ተነሡ
እናታችን መጣች አባ ጊዮርጊስም
ስሟን ስንጠራ መች ትቀራለች የተከዘን ልታጽናና
ነይ ሰንላት ትመጣለችና /2/
የጽጌው ማኅሌት በጸሎት ሲጀመር ማርያም ትመጣለች በደመና አየር
ንዒ ስንል በሰዓታት ልትባርከን ትመጣለች በእውነት /2/
ፍልሰታ ሲጀመር ቃል ኪዳን ገብታለች የሌሊት ውዳሴን ንዒን ትሰማለች
ሕጻናትን በበረከት ልትጎበኝ ትመጣለች በእውነት /2/
በፍጹም ቸርነት እንዲምረን ጌታ በአማላጅነትሽ ሁኚልን መከታ
እናታችን አለችን እንድናለን ድንግል አንቺን ይዘን /2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.