የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም

St. Virgin Mary

ውዳሴ ማርያም

Lyrics

ውዳሴ ማርያም እጮሃለሁ ድንግል እናቴን እጣራለሁ

እንደ አባ ኤፍሬም ነይ ባርኪኝ ወድሰኒ ልጄ በይኝ

ውዳሴ ማርያም በሠርክ ጸሎት ላይ ዜማ ስናደርስ

ድንግል ትመጣለች ከቤተ መቅደስ

የብርሃን ምንጣፍ ከፊቷ ተነጥፏል

ቅዱስ ኤፍሬም ታጥቆ ያመሰግናታል

ውዳሴ ማርያም አባ ሕርያቆስም ምስጋና ያደርሳል

የቅዳሴው ዜማ ልብን ይመስጣል

በጎ ነገር ልቤ አወጣ እያለ ዳዊት በገናውን እየደረደረ

መሠረት ነሽና ውዳሴ ማርያም ለንጽሕናችን ንዒ ድንግል ይላል

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening