የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም

St. Virgin Mary

የጠሩሽ

Lyrics

በወርቅ ዙፋን ላይ ተቀምጠሽ ሳይሽ ልቤ ተሰወረ ድንግል በግርማሽ

የጠሩሽ አንቺን ተማጽነው የዳኑብሽ

የበላዔ ሰብእ እመቤት የአምላክ እናት

ድንግል አዛኝቱ ማርያም ቅድስት /2/

በቃል ኪዳንሽ ብዙዎች ድነዋል

በምልጃሽ ጽድቅን አግኝተዋል

የአምላክ ቸርነቱን አይተዋል /2/

የእሳት ባሕርን በንቺ ተሻግረዋል

የሰይጣንን ጾር በአንቺ ድል ነስተዋል

ለሰማያዊው ክብር በቅተዋል /2/

ነፍሳቸውም ጽድቅን አግኝታለች

ሕይወታቸውም በአንቺ ትድናለች

ድንግል ሆይ አትጣይኝ ትላለች /2/

እኔም በአንቺ እታመናለሁ

የአምላክ እናት አሳስቢኝ እላለሁ

በአማላጅነትሽ እድናለሁ/2/

እኛም በአንቺ እንታመናለን

የአምላክ እናት አሳስቢ እንላለን

በአማላጅነትሽ እንድናለን /2/

ምእመናንም በአንቺ ያምናሉ

የአምላክ እናት አሳስቢ ይላሉ

በአማላጅነትሽ ይድናሉ /2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening