የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም

St. Virgin Mary

ደስ ይበልሽ

Lyrics

ደስ ይበልሽ /2/ ዝናብ የታየባት

ወዳናለች ድንግል የታተመች ገነት

ክብር ለሆነችው ኑ እንዘመርላት

ደስ ይበልሽ እንበል ለብርሃን እናት

ማርያም ንጽሕት ድንግል ደስ ይበልሽ

ከሴቶቹ ሁሉ የተባረከሽ ነሽ

ሰላም እልሻለሁ ማርያም ደንግል

እንደ ብሥራታዊው እንደ ገብርኤል

ለአንቺ የተሰጠሽ ሁለት ድንግልና

አንደኛው በሥጋ ሌላው በኅሊና

ከዓለም ሁሉ ሴቶች ንጽሕት በመሆንሽ

ሰማያዊው ምሥጢር የተገለጸልሽ

ለልዑል ማደሪያ ለመሆን የበቃሽ

የጌታችን እናት በጣም ደስ የበልሽ

ማርያም ስትጎበኛት ወደ ቤቷ ገብታ

ኤልሳቤጥ ዘመረች በመንፈስ ተሞልታ

በማኅፀኗ ያለው ዘለለ በደስታ

እኛንም ትጎብኘን ከጠዋት እስከ ማታ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening