✦
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
•St. Virgin Mary
ድንግል ማርያም
Lyrics
ድንግል ማርያም የእኛ አማላጅ ድንግል ማርያም የእኛ አማላጅ/2/
ከአብርሃም ዘር የተመረጠች በድንግልና ጌታን ወለደች
መሶበ ወርቅ የመና ሙዳይ ቤቴልሔም ሆይ እሙ ለፀሐይ
የካኅናቱ ወርቅ ማእጠንት የዕጣን መያዣ ነሽ ደግ ፍጥረት
የመለኮት አትሮንስ የኮሬብ ተራራ የወርቅ መቅረዝ የአሚናዳብ ሠረገላ
ንጹሕት የሠርግ ቤት የብርሃን ድንኳን የአምላክ ማደርያ ታቦተ ጽዮን
የአቤል የዋኅት የሴት ቸርነት የዮሴፍ አጽናኝ ርግብ የዋሂት
የአሮን ጸናጽል የጌዴዎን ፀምር የሰሎሞን ጥበብ የዳዊት መዝሙር
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.