የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም

St. Virgin Mary

አክሊለ ምክሕነ

Lyrics

አክሊለ ምክሕነ ወቀዳሚተ መድኃኒትነ ወመሠረተ ንጽሕነ /2/

ኮነ በማርያም ድንግል

የመመኪያችን ዘውድ የአዳም ተስፋ

የአምላክ እናቱ አማልጅን ከልጅሽ

ድንግል ወላዲቱ

የመመኪያችን ዘውድ በዓለም ተስበን

ፈጽሞ እንዳንጠፋ ምልጃሽ አይለየን

ድንግል የእኛ ተስፋ

የመመኪያችን ዘውድ የድኅነታችን መጀመሪያ

የንጽሕናችን መሠረት /2/

ተገኘልን በማርያም ድንግል

የመመኪያችን ዘውድ የሴም ቡራኬው

የይሰሐቅ መዓዛ ያዕቆብ እንዳየሽ

በፍኖተ ሎዛ

የመመኪያችን ዘውድ በቃል ኪዳንሽ

ለምንማጸንሽ የመመኪያችን ዘውድ የድል አርማችን ነሽ

የመመኪያችን ዘውድ የዳዊት በገና

የሰሎሞን አክሊል የታተምሽ ጉድጓድ

የታጠርሽ ተክል

የመመኪያችን ዘውድ ፋራን የምትባይ

የእንባቆም ተራራ በዓለም እንዳንጠፋ

ድንግል ሆይ አደራ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening