የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም

St. Virgin Mary

የኤልሳቤጥ ሐሴት

Lyrics

የኤልሳቤጥ ሐሴት የዮሐንስ ደስታ

የእኛንም ተቀበይ ውዳሴና እልልታ

እናታችን ማርያም ይድረስሽ ምስጋና

ሰላም ለአንቺ ይሁን የምሕረት ደመና

የሁላችን እናት ተስፋ ድኅነታችን

ወላዲተ አምላክ ድንግል ብርሃናችን

ያጣ ከቶ የለም አንቺኑ ለምኖ

ክብርን ያላገኘ በስምሽ ተማጽኖ /2/

የያዕቆብ መሰላል የአሮን በትር

በልባችን ይስረጽ ድንግል ያንቺ ፍቅር

እንደ ሕርያቆስ እምነት ባይኖረን

የምስኪኖች አጽናኝ አለሁ በይን /2/

ምሕረት እንድናገኝ ወድቀናል ከፊትሽ

ሸክማችን ይራገፍ በአማላጅነትሽ

ማን ጐድሎበት ያውቃል አንቺኑ ተማጽኖ

ሰላምን ያገኛል በጥላሽ ሥር ሆኖ /2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening