የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም

St. Virgin Mary

ወዳጄ ሆይ ተነሽ

Lyrics

ወዳጄ ሆይ ተነሽ ውበቴ ሆይ ነይ

ነይ በማለዳ ነይ እንድረሳው የዓለምን ሰቃይ

ቃልሽም መልካም ነው ፊትሽም ያማረ

መልክሽን አሳይኝ /2/ ድምጽሽን አሰሚኝ

እኅቴ ሆይ ሙሽራዬ ማረፊያ ገነት የኤዶም ምንጭ ነሽ የታተምሽ ሕይወት

ሙሽራዬ አንቺ የገነት ምንጭ የሕይወት ውኃ ጉድጓድ

ግርማሽ የሚማርክ /2/ ድምጽሽም የሚያርድ

የአባቶች ቅዳሴ የቅዱሳን መዝሙር

የክርስቲያን ሕብረት የምስጋና/2/ ዘይት

ሙሽራዬ ለእናቷ አንዲት ናት ለወለደቻት የተመረጠች ናት

ድንግል የሰላም እመቤት ወዳጄ ሆይ ነይ

የዋህ ርግብ ነሽ አምላክ ለድኅነት

ምክንያት መርጦ ያከበረሽ ሙሽራዬ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening