የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም

St. Virgin Mary

አንቺን የያዘ ሰው

Lyrics

አንቺን የያዘ ሰው ምን ይጎድልበታል

በምልጃሽ በረከት ቤቱ ሞልቶለታል

ዘር መከር ባይኖው ጎተራው ባይሞላ

ሁሉም ይሸፈናል በረድኤትሽ ጥላ

በረከትሽ ብዙ የደናግል ገንዘብ

የምስኪናን እናት የርሁባን ቀለብ

ለሁሉ መጋቢ ጸጋሽ የማይጎድል

ስምሽ ጥዑም ምግብ ከረሀብ የሚያስጥል/2/

አንቺ ብትመጪ ከምስኪኗ ቤቴ

እንደ መጥምቁ እናት በዛልኝ ሐሴቴ

የአዲስ ኪዳን ቁርባን መንበር ጠረጴዛ

ጽድቅን አሸተትን የሕይወትሽን መዓዛ /2/

ልቤ ተጠራጥሮ ኪዳንሽን ካልከዳ

ልመናም አልወርድም አልይዝም አቁማዳ

ሁሉን እየሞላሽ መመገብ ታውቂያለሽ

ቢዝቁት የማያልቅ ጸጋና ሀብት አለሽ/2/

የእግዚአብሔር ማረፊያ ኮረባዊት ዋሻ

የሕይወት ውሃ ምንጭ የህግ መፍሰሻ

ነበልባል ተዋህዶሽ ሙሴ አንቺን አይቷል

ጫማውን አውልቆ በፊትሽ ተደፍቷል/2/

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening