የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
•St. Virgin Mary
አወድሰኝ ኤፍሬም
አወድሰኝ ኤፍሬም ብላ ጠየቀችው ድንግል እናታችን
ባርክኒ ብሎ ወገቡን ታጠቀ ኤፍሬም አባታችን
የልጄ በረከት ይደርብህ ብላው ጀመረ ምሥጋና
ወደ ብርሃን ድንኳን ወደ ተከበረው ደራሲው ገባና /2/
ልቡ ያዘነ አዳምን ሊያድን ጌታ ወደደ
ዳግሚት ሰማይ ማደሪያው ልትሆን እርሱ ፈቀደ
የሰማይ ምስጢር በማኅጸንሽ ተከናወነ
ከዘሩ ቀርተሽ በንጽሕናሽ የሰው ዘር ዳነ
ሰአሊ ለነ ሰአሊ ለነ
አዕምሮውን ልቡን ሳይብን አሳድሪብን
ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን
በሔዋን ምክንያት በለሷን በልተን ገነት ቢዘጋ
በአንቺ እናትነት ዳግም ተዛመድን ከአምላካችንጋ
ትውልድ ሁሉ ስምሽን በክብር አመሰገነ
የሲዖል ቀንበር በላያችን ላይ ስላልተጫነ
ሰአሊ ለነ ሰአሊ ለነ
አዕምሮውን ልቡን ሳይብን አሳድሪብን
ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን
የዕዳ ደብዳቤ ተቀዳደደ የባርነቱ
አዳም ሔዋንም ከእስራታቸው ወጡ ተፈቱ
የሲዖል ጽልመት በልጅሽ ጠፍቶ ብርሃን እረፍት አገኘን
የምሕረት ዓመት በአንቺ ዘመነ
ሰአሊ ለነ ሰአሊ ለነ
አዕምሮውን ልቡን ሳይብን አሳድሪብን
ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን
ሙሴ በሲና ሳትቃጠይ ያየሽ ሐመልማል
እግዚአብሔር መርጦሽ በማሕጸንሽ ዙፋኑን ተክሏል
የዲያብሎስን ጥበብ እንዲያፈርስ አምላክ ሰው ሆነ
በልጅሽ መሞት መዳናችንም ተከናወነ
ሰአሊ ለነ ሰአሊ ለነ
አዕምሮውን ልቡን ሳይብን አሳድሪብን
ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.