የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም

St. Virgin Mary

እመቤታችን በቀኝ ቆማለች

Lyrics

እመቤታችን በቀኝ ቆማለች

የብርሃን ልብሷን ተጎናጽፋለች

ሰአሊተ ምሕረት መዝገበ ጸሎት

አቁራሪተ መዓት የጌታዬ እናት /2/

እመቤታችን የብርሃን ልብስሽን

ነይ ተጎናጽፈሽ ንዒ ሥንልሽ

ሠዓታቱን ሥናደርስ

በሠጠሽ ቃል ኪዳን እንድታስምሪን

እንለምንሻለን ከእግርሽ ሥር ወድቀን

እመቤታችን ከኪሩቤል ድንግል አንቺ ትበልጫለሽ

ከሦስቱ አካል አንዱን ወልድን ስለወለድሽ

ስለዚህ ድንግል ሆይ እንወድሻለን

ዘወትር ጠዋት ማታ እንማልዳለን

እመቤታችን ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና

እናት እንድትሆኚኝ ሸልሞኛልና

ስምሽን ስጠራ ሠዎች ያዝኑልኛል

ሞገሴ ነሽና ይድረስሽ ምሥጋና

እመቤታችን ድንቅ ድንቅ ነገር

ነቢያት ተናገሩ ሀገረ እግዚአብሔር ድንግል ናት እያሉ

ሁለተኛው አዳም ከአንቺ ተወለደ

የተዘጋው ደጃፍ በአንቺ ተከፈተ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening