✦
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
•St. Virgin Mary
ኪዳነምሕረት እመቤት
Lyrics
ኪዳነ ምሕረት እመቤት እመቤት /2/
ነይልን /2/ ካለንበት /2/
ከሰማያት በላይ ካለው ከማደርያሽ /2/
ዝማሬ ከሞላው ከዘለዓለም ቤትሽ
የምድር ፍጥረታት ማርያም ማርያም ሲሉሽ /2/
የቃል እናት እመቤቴ ነይ በሠረገላሽ/2/
ከፀጥታ ወደብ ከፍቅር አውድማ /2/
ከሰላሙ መንደር ከእውነት ከተማ
ሰአሊ ለነ ቅድስት ውዳሴሽ ሲሰማ /2/
ከሚካኤል ከገብርኤል ጋር ነይልን ከራማ /2/
ዘርፋፋው ቀሚስሽ ይውረድ ከሰማያት/2/
ዕንባችን ይታበስ በአንቺ አማላጅነት
የጽዮን ዘማሬ ተሞላ ነፍሳችን /2/
ንዒ /3/ እንበል እንደ አባቶቻችን /2/
ፍጥረታት ሊድኑ በአማላጅነትሽ /2/
የዘላለም ኪዳን አማኑኤል ሰጠሽ
ትውልድ ይህን አምኖ ብጽዕት ይልሻል /2/
እናቴ መመኪያዬ ምርኩዜ ሆነሻል /2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.