✦
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
•St. Virgin Mary
ድንግል ሆይ ወደ እኔ
Lyrics
ድንግል ሆይ ወደ እኔ ትመጪ ዘንድ እንዴት ይሆናል
እመቤቴ ወደ እኔ ትመጪ ዘንድ እንዴት ይሆናል
ደካማ ነኝ እኔ ምግባር ይጎለኛል /2/
በሥጋዊ ሳይሆን በመንፈስ አይኖቼ
ለማየት እሻለሁ ከልቤ ጓጉቼ
ስራዬ የከፋ መሆኑን አውቃለሁ
ስምሽንም መጥራት እጅግ እፈራለሁ
ክብርሽ የበዛ ነው ቤዛዊተ ኩሉ
ምሕረት ታሰጫለሽ ላመነብሽ ሁሉ
ባንቺ የተመካ ምንም አያገኘው
የገሀነም እሳት ሲዖልም አይነካው
የልዑል ማደሪያ የሲና ዕፀጳጦስ
አንቺን ላመስግንሽ ከደዌ እንድፈወስ
ፍቀጅልኝ ድንግል ካንቺ ጋር እንድኖር
ልጅሽን ማልጅልኝ እንዲያበቃኝ ለክብር
ምንም ተስፋ የለኝ ያላንቺ እናቴ
እመካብሻለሁ እስከ እለተ ሞቴ
የምስኪኖች አጽናኝ የችግር ቀን ደራሽ
የልቤ ማረፊያ ምግቤ መጠጤ ነሽ
የጌታዬ እናት ድንግል እመቤቴ
ተጠብቃ ትኑር ባንቺ ዘንድ ህይወቴ
የትህትናሽ ምንጭ የፍቅር ውቅያኖስ
ጠጥቼ ልርካብሽ ድንግል እንድቀደስ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.