የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም

St. Virgin Mary

ትምክሕተ ዘመድነ

Lyrics

ትምክሕተ ዘመድነ /2/ ማርያም እምነ ማርያም

ትምክሕተ ዘመድነ

የድኅነታችን አርማ የነጻነታችን

የሕይወት መሰረት ነሽ ድንግል እናታችን

አንችን ለኛ ዘርን ባያስቀር እንደ ጥንቱ እንደ ሰዶም ምድር ሁላችንም በጠፋን ነበር

የአብርሃም ድንኳን ነሽ አምላክ ያደረብሽ

የጌዴዎንም ጸምር ለይቶ ያከበረሽ

የኛ ቤዛ በጉ የተያዘብሽ የዋኅ ርግብ

ከአበው ሥር የተገኘሽ እፀ ሳቤቅ የሕይወት ሐረግ ነሽ

አምላክ ከሰማይ ሆኖ ይህችን ዓለም ሲቃኝ

ንጽሕት ቅድስት ሆነሽ ማርያም አንቺን ቢያገኝ

ትኅትናሽን ሕይወትሽንም ወዶ

ቃል ሰው ሆነ ከሰማያት ወርዶ

አከበረሽ በፍጹም ተዋህዶ

የመዳናችን ምክንያት የሰው ልጆች ሰላም

ከኃጢአት ከመርገም የዳነብሽ ዓለም

አምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን

በሲዖል ውስጥ ተግዘን የኖርን

ድንግል ባንቺ ነፃነት አገኘን

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening