የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም

St. Virgin Mary

እናታችን ጽዮን

Lyrics

እናታችን ጽዮን ይድረስሽ ምስጋና

መጠጊያ ማረፊያ ጥላችን ነሽና

ከገነት ብንወጣ ማረፊያ ሆንሽን

የምሕረት ደመና ውኃ ሰጠሽን

የሕይወት እንጀራን አመጣሽልን

በአሥራትም በአደራም ለአንቺ ተሰጠን

የኤልሳቤጥ አጽናኝ የጭንቅ ቀን ደራሽ

የኃጢያታችን ብዛት ዳገት ሳይሆንብሽ

ምሥራችን ደስታ ይዘሽልን መጣሽ

ማርያም ስንልሽ ደረስሽልን ፈጥነሽ

ውለታሽ ብዙ ነው ከልብ የማይጠፋ

ስምሽ መጽናኛ ነው አዝኖ ለተከፋ

በእንተ ማርያም ብሎ ለለመ

የሰማይ የምድሩም ማንም አልጨከነ

በትራችን አንቺ ነሽ የምትደግፊን

ባሕረ እሳትን የምታሳልፊን

ጽርሐ ሥላሴ ነሽ ማኅደረ መለኮት

ሁል ጊዜ አንጠግብሽም እንላለን ብጽእት

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening