✦
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
•St. Virgin Mary
ማርያም እመቤቴ
Lyrics
ማርያም እመቤቴ የአምላክ እናት
ማደሪያ የሆንሽው ዙፋን ለመለኮት
ከሴቶች ሁሉ አንቺ ነሽ የተባረክሽ የነጻሽ በእውነት
ከቶ እንደምን ቻልሽው መድኃኔዓለምን
ሰማይና ምድር የማይችሉትን
ለዚህ የተመረጥሽ ታላቋ እድለኛ
ምሕረትን ከልጅሽ ለምኝልን ለእኛ /2/
ምንኛ ድንቅ ነው ምሕረቱ የወልድ
የአንቺን ሥጋ ለብሶ ሲሆነን ዘመድ /2/
ከዙፋኑ ወርዶ ሰው የሆነብሽ
የሕይወት ሙሽራ ማርያም አንቺ ነሽ
የነቢያት ሞገስ የሐዋርያት የሰማዕታት አክሊል የፃድቃን እናት
የኛ መመኪያችን የሐጥአን ተስፋ
ወልድን በመውለድሽ ሀዘናችን ጠፋ /2/
ቅዱሳን በገነት ሲያመሰግኑሽ
መላእክት በሰማይ ሲያገለግሉ
እኛም የአዳም ልጆች ከመሬት ሆነን
ሰአሊ ለነ ቅድስት እንልሻለን /2/
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.