✦
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
•St. Virgin Mary
እመ አምላክ
Lyrics
እመ አምላክ /2/ አስቢኝ በሰርክ
ሐዘኔ ጭንቀቴ በጣም በዛብኝ
ከልጅሽ አስታርቂኝ አንቺው አማልጅኝ
ከመንበሩ ቆመሽ ንገሪው ለልጅሽ
እናቱ ነሽና እሱ አያሳፍርሽ
እኔ ኃጢያተኛው በደሌን አውቃለሁ
ምርኩዜ ነሽና እከተልሻለሁ
መንገዱ ጠፍቶብኝ የጽድቁ ጎዳና
መብራቱን አብሪልኝ እመጣለሁና
መመገብ ይቅርብኝ አልራብምና
ስምሽን ስጠራው እጠግባለሁና
አበው ሊቃውንቱ በአንቺ ይመካሉ
እመ አምላክ እያሉ ስምሽን ይጠራሉ
ከገሀነም አውጪኝ ከዚያ ነበልባል
ከሲዖል ወድቄ እንዳልቃጠል
ያ የስቃይ ሀገር ባሕሩ ያሰጥመኛል
አንቺ ከለመንሽው ልጅሽ ያዝንልኛል
ወገን አታድርጊኝ ከሲዖል ከተማ
መድረሻ አያሳጣኝ የእሳቱ ጨለማ
አወድስሻለሁ በኤፍሬም ውዳሴ
ሁኝልኝ ጠበቃ አደራ ለነፍሴ
እኔስ እፈራለሁ ምግባሬን ሳየው
ደካማው እምነቴ እየለየኝ ነው
አልረሳሽም ድንግል እማፀንሻለሁ
አማላጅነትሽ መድኅን ነው አውቃለሁ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.