✦
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
•St. Virgin Mary
ከፈጣሪ በታች
Lyrics
ከፊጣሪ በታች ከፍጡራን በላይ 2/
ማን አለ እንደ አንቺ ድንግል ንጹሕ በዓለም ላይ
ኦ/3/ ድንግል ማርያም ዘለዓለም መኩሪያዬ ነሽ መመኪያዬ /2/
አምላክ ለማደሪያው መርጦ ያዘጋጀሽ /2/
ጽዮን የተባለች ሀገር ድንግል ሆይ አንቺ ነሽ
በሀሳብሽ ድንግል ድንግል በሥጋሽ /2/
ከፍጥረታት ሁሉ ለአንቺ ምሳሌ የለሽ
ፍቅሩ ለዘለዓለም የማይጠገበው /2/
ከስም ሁሉ በላይ ጣፋጭ ድንግል የአንቺ ስም ነው
በዕዝራ መሰንቆ በዳዊት በገና /2/
ይገባሻል ለአንቺ ድንግል ሁል ጊዜ ምስጋና
እስኪ ልያዝና ደጋፊ ምርኩዜን
እስኪ ልያዝና የረሀብ መድኃኒቴን
ወደ አምላክ ቤት ልሒድ ልቀጥል ጉዞዬን
ለፍርድ ስጠራ በደለኛዋ እኔ
ለፍርድ ስጠራ በደለኛው እኔ
የእኔ መማጸኛ ድንግል ቁሚልኝ ከጎኔ
🙏 Help improve these lyrics
Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.