የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም

St. Virgin Mary

ዳግሚት አርያም

Lyrics

የአባ ሕርያቆስ ድርሳነ ቅዳሴው

የእነ አባ ኤፍሬም ኃይለ ጸሎታቸው

ማርያም ድንግል ነሽ የእምነት ሙዳያቸው

ወይነ ሕይወት ክርስቶስ የተመላብሽ

ጽዋዐ መድኃኒት ነውር የሌለብሽ

የማይቻለውን በማኀፀን የቻልሽ

ምንኛ ድንቅ ነው መቅደስነትሽ

አርፌም አልተኛ ዙፋኔን ትቻለሁ

የያዕቆብን አምላክ ማደሪያ ካላየሁ

ብሎ የናፈቀሽ ዳዊት አባትሽ

ኢያቄም ወሐና ገና ሳይወልዱሽ

እንደምን ታደሉ ሐናና ኢያቄም

የእነርሱ ናትና ዳግሚት አርያም

በሥጋዊ ፈቃድ ሊያስገኙሽ ያልቻሉ

የእግዚአብሔር ስጦታ መድኃኒተ ኩሉ

የድኅነት ምልክት የምዕመናን ዓርማ

ተናጋሪ ገነት የጻድቃን ከተማ

ማኅደረ መለኮት የአብ ቃል መገኛ

የሕይወት ውኃ ምንጭ የአዳም ዘር መዳኛ

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening