የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም

St. Virgin Mary

ንጽሕት ቅድስት

Lyrics

ንጽሕት ቅድስት የተመረጥሽ

የመንፈስ ኃይል የጸለለሽ

የእግዚአብሔር ቃል ያደረብሽ

ለእኛ ሕይወት መዲና ነሽ

በጣም /3/ ቅድስት ማርያም

ክብርት ነሽ ምልዕተ ጸጋ

እናታችን ልዕልት ነሽ እመቤታችን

የሕይወት አምባ መጠጊያችን

የዘለዓለም አለኝታችን

ኆኅተ ምሥራቅ የአምላክ መንበር

የሕይወት ቤዛ ድንቅ ምስጢር

የኃጥኣን ተስፋ የአምላክ ሀገር

ቅድስት ነሽ የእኛ ክብር

🙏 Help improve these lyrics

Found a mistake or have a better version? Your contribution helps the community.

✍️ Contribute
🎵Select a Mezmur to begin listening